
መስከረም 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
መሪዎቹ በጋራ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡
መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በድጋሚ በመመረጣቸውም የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውን የኢሚሬት ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ