
ባሕር ዳር፡ መስከረም 19/2012 ዓ/ም (አብመድ) ዓለም አቀፍ የሲቪል አቬሽን ድርጅት ከተመሠረተ 75ኛ ዓመቱ ነው፤ በጉባኤውም ከመሥራች ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ተወክላ እየተሳተፈች ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ እያበረከተች ላለው አስተዋጽኦ በተለይም በ‹ኢንተርናሽናል ሬቨኑ ፓሴንጀር ሬት› 90 ከመቶ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ 36 የዓለም ሀገራት ውስጥ አንዷና በአፍሪካም በቀዳሚነት ደረጃ የምትገኝ መሆኗ በጉባኤው መነሳቱትን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በማኅበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡