ጦርነት ባለባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደገጠማቸው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ አስታወቁ።

464
አዲስ አበባ፡ መስከረም 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለተጎጂዎች ለማቅረብ ቢታሰብም ሁኔታዋች አሰቸጋሪ እንደሆኑባቸው የእንግሊዝ መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ ተናግረዋል። የእንግሊዝ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ልዩ አማካሪ በጦርነት ቀጣና ውስጥ ባሉ የአማራ ክልል አካባቢዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ጦርነቱ ንፁሃንን ለሞት፣ ለእንግልት እና ለስደት መዳረጉን ገልጸዋል።
ጦርነት ባለባቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃን ዜጎችና ምንም የማያውቁት እንስሳትም ጭምር ተገድለዋል፤ በርካታ ወገኖች ለአካል ጉዳት እና ለስደትም ተዳርገዋል፤ መሠረተ ልማቶችም ወድመዋል።
“ይህን ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በአካል ሄደን በዓይናችን አይተናል፤ አዝነናልም” ብለዋል ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት የእንግሊዝ መንግሥት የሰብዓዊ ደጋፍ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ሚስተር ኒክድል። ሚስተር ኒክድል ሕጻናት ጭምር ለሞት እና ለጉዳት መዳረጋቸውን አንስተዋል፡፡
የእንግሊዝ መንግሥት ለማንም የማድላት ፍላጎት የለውም ያሉት ልዩ መልዕክተኛው ተቀዳሚና መሠረታዊ ትኩረቱ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው ባለፈው ዓመት ለትግራይ ክልል በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ መንግሥታቸው 136 ሚሊዮን ዶላር ወጭ ማድረጉንም አንስተዋል።
በተመሳሳይ በጦርነቱ ምክንያት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ተጎችዎችን ለመርዳት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው የተናገሩት። ልዩ መልዕክተኛው ከጉብኝታቸው መልስ መንግስታቸው ለተጎጅዎች ድጋፍ ለማድረግ እና የበኩሉን እገዛ ለማድረግ እንደሚሰራም አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት በተለያየ የሥራ ኃላፊነት በሚኒስትርነት በእጩነት የቀረቡ
Next articleበአዲስ የተመሠረተው መንግሥት የሕዝብን ሰላም በማረጋገጥ ከድህነት የሚያወጣ መሆን እንዳለበት የጎንደር፣ የደሴና የደብረ ማርቆስ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡