
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሄዳል። ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24/2014 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያዳምጣል።
በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል።
በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ የዕለቱን ልዩ ስብሰባ ያጠናቅቃል።
ልዩ ስብሰባው ከረፋዱ 3:30 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋናው አዳራሽ እንደሚካሄድም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ