
ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በአማራ ክልል በአሸባሪዉ የትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ ይህ ድጋፍ በመላው የተቋሙ አመራርና አባላት ስም በመደረጉ መደሰታቸውን ገልጸው በየትኛዉም ክልል የሚደርስ ጉዳት የኛም ጉዳት ነዉ ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የኤጀንሲዉ አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ለመከላከያ ሠራዊት ደጋፍ ከማድረጋቸውም ባሻገር ደም መለገሳቸውን አስታውሰው ከዚህ ባለፈ የኤጀንሲዉ አባል ሆነዉ የመዝመት ጥያቄ ላቀረቡ አባላትም አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ መላካቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ሌሎች ክልሎች ኤጀንሲው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸዉ በወራሪዎች ግፍ የተነሳ ስቃይ እና እንግልት እየደርሰበት ለሚገኘው ሕዝብ ኤጀንሲዉ ድጋፍ በማድረጉ በአማራ ክልል ሕዝብ፣ በክልሉ መንግሥት ስም እና በተፈናቃዮቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በአሁኑ ሰዓት 500 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸዉን ርእሰ መስተዳደሩ ገልጸው በኤጀንሲው የተደረገው ድጋፍ ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት ቀየ ለመመለስ አሰተዋጽኦ ያበረክታል ማለታቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m