የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሄዳል።

152

ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሄዳል። ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24/2014 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያደምጣል።

በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል።

በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ የዕለቱን ልዩ ስብሰባ ያጠናቅቃል።

ልዩ ስብሰባው ነገ ከጧቱ 3:30 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋናው አዳራሽ እንደሚካሄድም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአዲስ የተመሰረተዉ መንግሥት በሕዝብ እንደራሴዎች እና በ6ኛው የመንግሥት የምሰረታ ጉባዔ በተሳተፉ ተጋባዥ እንግዶች እይታ…
Next articleኤጀንሲው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።