ለዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ አሸኛኘት ተደረገላቸው።

201
ለዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ አሸኛኘት ተደረገላቸው።
ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በዓለ ሲመት ላይ የታደሙት የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ ወደ ሀገራቸው አቅንተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዚዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በአሸኛኘት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየፌዴራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ከሰሜን ወሎ ተፈናቅለው በደሴ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
Next articleለናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ቡኻሪ አሸኛኘት ተደረገላቸው።