
አዲስ አበባ፡ መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ላይ ታድመው ዛሬ ወደ ሀገራቸው አቅንተዋል።
በወቅቱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዝዳንቱ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በአኛኘት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተሳትፈዋል።





በተያያዘም የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ ትናንት ምሽት ወደ ሀገራቸው ሲያቀኑ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ