
መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የትናንቱ በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታ የጋራ ግብረኃይል አስታወቀ፡፡
መስቀል አደባባይ የተከናወነው ሥነ-ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማችን ነዋሪዎች ላሳዩት ጨዋነት
ለተሞላበት ቀና ትብብር ግብረኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ትናንት መስከረም 24/2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ በአዲስ መንግሥት ፣ በአዲስ ተስፋ አዲስ ምዕራፍ የምትጀምርበት ቀን ነው።
የጋራ ግብረኃይሉ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከብሔራዊ መረጃ ደኅንነት፣ ከመከላከያ ሠራዊትና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር አስቀድሞ ዕቅድ በማውጣት እና ኅብረተሰቡን በማስተባበር የተከናወኑት ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል፡፡
የአዲስ ምዕራፍ በዓለ- ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታ የጋራ ግብረኃይሉ አስታውቋል፡፡
ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅም በፍፁም
ሙያዊ ብቃት ኃላፊነታቸውን የተወጡ ለመላው የጸጥታ አካላትና ለሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች የጸጥታ የጋራ ግብረ-ኃይል ከፍ ያለ ምስጋናውን በታላቅ አክብሮት ያቀርባል ብሏል በመግለጫው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
