
የ17ኛው የዶሃ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3ኛው ተጓዥ ምድብ ዛሬ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ኳታር ዶሃ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል፡፡
17 የልዑካን አባላት ያካተተው ይህ ምድብ
የ1500 ሜትር ወንድና ሴት፣ የ5000 ሜትር ሴት እና
3000 ሜትር መሰናክል ወንድ አትሌቶች እንዲሁም አሰልጣኞችና የማሳጅ ባለሙያዎችን የያዘው ነው።
ልዑኩ በስፍራው ሲደርስ የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ተገኝተው ተቀብለውታል፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን