ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

316

ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ መላካቸውን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር አስታወቁ።
ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል እንዳስታወቁት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ፤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ በመፈጸማቸው በራሳቸው እና በሚመሩት ሕዝብ ስም መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ እና አስመራ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከግጭት እና ከፍጥጫ በመውጣት ሰላምና ወዳጅነትን መመስረታቸው ለአፍሪካ ቀንድ አዎንታዊ ማመላከቻ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን አቶ የማነ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በሁሉም፣ ከሁሉም፣ ለሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን የመገንባት ሕልም ለስኬት እንዲበቃ እንሠራለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleበዓለ-ሲመቱ በሰላም መጠናቀቁን የጸጥታ የጋራ ግብረኃይል አስታወቀ።