
መስከረም 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ መንግሥት ምስረታ እና በዓለ ሲመት ላይ የተገኙት የጅቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኡመርጌሌህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በጎረቤት ሀገራችንና ወንድም በኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚመሰረተው አዲስ መንግሥት በዓለ ሲመት ተገኝቼ የደስታ መልዕክት ሳስተላልፍ እጅግ ደስታ ይሰማኛል ነው ያሉት፡፡
ዶክተር ዐቢይ አሕመድና የኢትዮጵያ ሕዝብንም እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ፕሬዚዳንቱ በራሴና በጅቡቲ ሕዝብ ስም የተሰማኝን ደስታም ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የጅቡቲ መንግሥትና ሕዝብም ከኢትዮጵያ ጎን ይቆማል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በረጅም የሀገረ መንግሥት ምስረታ ታሪኳ የፓን አፍሪካን አጀንዳዎችን በማቀንቀን ከፍ ብላ የምትታወስ ሀገር ናትም ብለዋል፡፡
በአፍሪካ የመጀመሪያዋ የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል በመኾንም ሀገራዊ አጀንዳዎች እንዲነሱ ያደረገች፤ የአፍሪካ ሕብረት መሥራችና ለአፍሪካ ሀገር እድገት ወሳኝ ቁልፍ ሚና ያላት ሀገር ናት ሲሉም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ፣ የሃይማኖት ብዝኃነትን የምታስተናግድ እና ሕብረ ብሔራዊ ሀገርም ናት ሲሉም የጅቡቲው ፕሬዝዳንት በበዓለ ሲመቱ ተናግረዋል፡፡
ዛሬም ኢትዮጵያ ለሰላሟ በጋራ የሚተጉ ሕዝቦች አሏት፤ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ የጅቡቲ ሕዝብ እና መንግሥትም ከኢትዮጵያ ጎን መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
በአዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ