
ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የዩጋንዳ ሕዝብ ስም ለአዲስ መንግሥት ምስረታ አደረሳችሁ ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለ60 ዓመታት የአፍሪካ የፖለቲካ ተሳትፎዬ በዩጋንዳ ጭምር ያስተዋልኩት እና የታዘብኩት ችግር የጎሳ ፖለቲካ ነው ብለዋል፡፡ በዩጋንዳም እኔ የዚህ ጎሳ ነኝ ወይም የዛኛው ጎሳ ነኝ፤ እኔ ከዚህኛው ወይም ከዛኛው ሃይማኖት ነኝ የሚለው የጎሳ ፖለቲካ ለበርካታ ችግር ዳርጎናል ብለዋል፡፡ ሙሴቬኒ ይህንን አይነቱን ችግር ለመፍታት ዩጋንዳ የአንድነት እና በሀገር ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖለቲካን ማራመድ መጀመሯን ገልጸዋል፡፡
እናም ኢትዮጵያውያንም ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ በአንድነት እና የሕዝብን ጥቅም የሚያከብረውን መንገድ ልብ እንዲሉት ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የሁላችን እናት ናት ነው ያሉት፡፡ አንድ ቀን በጥልቀት እንደሚጎበኟትም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምራ ደቡብ ሱዳንን ስትደገፍ እንደነበር ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ውጭ አንድ ቀን ማደር አትችልምም ብለዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ያለ ኢትዮጵያ አሸናፊ ልትሆን እንደማትችልም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን የሰላም ምንጭ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡
ከንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ድጋፍ ስታደርግ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ በተለያዬ አቅጣጫ ጦርነት ላይ የነበሩት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ታላቅ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ ከመንግሥቱ በኋላ የመጡ የኢትዮጵያ መሪዎችም ድጋፋቸው አለመለየቱን ነው የገለፁት፡፡ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ጋር በሰላም ነጻነቷን እንድታገኝ ኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓንም ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን በየትኛውም ጊዜ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትሆንም አረጋግጠዋል፡፡ ታናሽ ወንድሜ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ ያለህም ብለዋቸዋል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው እና ታርቆ ክንዴ