
መስከረም 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታ እና መክፈቻ ጉባዔ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር ለተመረጡ የምክር ቤት አባላት ለዚህ ከፍተኛ ኀላፊነት ስለመመረጣቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የተመረጡበት ወቅት ለሀገሪቱ ልዩ በመሆኑ የስኬት የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ እዚህ ለመድረስ ብዙ ዋጋ መከፈሉን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ ለዚህ አዲስ ምዕራፍ መባቻ ላይ ለመድረስ መስዋእትነት የከፈሉ ውድ ኢትዮጵያውን ክብር እንደሚገባቸውም ፕሬዝዳንቷ አንስተዋል፡፡
የምክር ቤቶቹ አባላት የመረጣቸውን ሕዝብ ፍላጎት ማወቅ እና በምክር ቤቶቹ ተመራጮች ቃል የገቡትን እንዲፈጽሙ እንደሚከታተሉ እምነታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፓርላማ የሕዝብን የልብ ትርታ ለማወቅ እድል ያለው ነው፤ በየጊዜው እያደጉ የሚመጡ የሕዝብ ፍላጎቶችን ለማወቅ እድል ይሠጣል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ “ምክር ቤቶቹ የሕዝብ ስሜት የሚንጸባረቅበት፣ የሚስተጋባበት፣ የተለያዩ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት፣ የሚፋጩበት፣ ተከራክረው የሚያሸንፉበት ቦታ መሆን ይጠበቅባቸዋል” ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ