“ባለፉት ዓመታት የሀገራችንን እድገትና ሰላም በማይፈልጉ የውስጥ ተላላኪዎችና በውጪ ሀገራት ጠላቶች ተፈትነናል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

94
ባሕር ዳር፡ መስከረም 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሀገራችንን እድገትና ሰላም በማይፈልጉ የውስጥ ተላላኪዎችና በውጪ ሀገራት ጠላቶች መፈተኗን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡
ታላላቅ ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ ሚዲያዎችም ኢትዮጵያ ፈርሳለች በማለት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሰራጩ ቆይተዋል ነው ያሉት፡፡
በሌላ በኩል በዚህ ክፉ ጊዜ በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያን ለማሻገር ሌትከቀን ሲሠሩ እንደቆዩ አስረድተዋል፡፡
በ6ኛው ክልላዊና ሀገራዊ ምርጫ የሰላምና የዴሞክራሲ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በጨዋነታና በአርቆ አሳቢነት የተሳተፉበት ወዳጆቻችን የተደሰቱበት ነገር ግን ጠላቶቻችን ያፈሩበትና አንገታቸውን የደፉበት ክስተት ሆኖ አልፏል ብለዋል፡፡
በሕዝብ የተመረጠው መንግሥትም በየደረጃው ባካሄደው የመንግሥት ምስረታ ውስጥ ሁሉንም አካታች በሆነ መልኩ አስፈፃሚ አካላትን ለማዋቀር ጥረት በመደረጉ ሀገራችን አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለመጀመር ቁርጠኝነቷን ለዓለም ማኅበረሰብ ያሳየችበት ወቅት ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ አባሳንጆ ኢትዮጵያ በምትመሰርተው መንግሥት ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።
Next articleበጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ለመታደም የጅቡቲ ፕሬዚዳት እስማኤል ኦማር ጌሌህ አዲስ አበባ ገቡ።