
መስከረም 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ አባሳንጆ ኢትዮጵያ በምትመሰርተው አዲስ መንግሥት ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚደንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።
ከሰዓታት በፊትም የወቅቱ የናይጀሪያ ፕሬዚደንት ሙሐመድ ቡሐሪ ኢትዮጵያ በምትመሰርተው አዲሱ መንግሥት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።
አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያ እና ናይጀሪያ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት ናቸው ።
የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ልዑኮቻቸው ኢትዮጵያ በይፋ በምትመሰርተው አዲስ መንግሥት መርኃግብር ላይ ለመታደም አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ባካሄደችው 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ አዲስ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል የአብላጫ ድምጽ ማግኘቱም ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m