
መስከረም 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ35ኛ ዙር ሰልጣኞች የስልጠና መክፈቻ ሥነ ሥርዓት አከናውኗል፡፡
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና ኣዛዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ ❝እኛ እያለን ሀገራችን አትደፈርም በማለት በአንድነት መንፈስ፣ በቁጭትና በሞራል በመነሳሳት ወኔና ጀግንነት ተላብሳችሁ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላት የሆነውን የሽብርተኛ ቡድን በፅናት ለመፋለምና ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም የሚሰጣችሁን ስልጠና በአግባቡ በመወጣት የጠላትን አንገት በማስደፋት ለወገን መከታ፤ አለኝታና ኩራት መሆን አለባችሁ❞ ብለዋል።
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለስልጠና ኃላፊ ኮሎኔል ተዝገራ ከበደ በበኩላቸው በማሰልጠኛ ቆይታችሁ የሚሰጣችሁን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመሰልጠን፣ በቆራጥነትነትና በጠንካራ ወታደራዊ ዲስፕሊን ሰልጠናውን በማጠናቀቅ ለሕዝብና ለሀገር የገባችሁትን ቃል ልታረጋግጡ ይገባል ነው ያሉት።
ምልምል ሰልጣኞች እንዳሉት ለሀገር ሉዓላዊነት ውድ ህይወቱን ከሚሰጠው ጀግና ሠራዊት ጎን ለመቆም ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርቱ ቤቱ በመምጣታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የሚሰጣቸውን ወታደራዊ ስልጠና በቁርጠኝነት ሰልጥነው የሽብርተኛውን የትህነግ ኃይል ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
መረጃው የተገኘው ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት https://.www.ameco.et
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ኤክስ (ትዊተር) https://bit.ly/336LQaS