6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

340

አዲስ አበባ: መሰከረም 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ መስከረም 24/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በላከው መግለጫ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ጉባኤ ላይም ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ፤ የጉባኤው ሂደትም የምልክት ቋንቋን ጨምሮ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል፡፡

በጉባኤውም በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመስራች ጉባኤው ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleዩኒቨርሲቲዎችና የፍትሕ ተቋማት ሽብርተኛው ትህነግ የፈጸማቸውን ወንጀሎች በጥልቀት በማጥናት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቅ እንዳለባቸው የሕግ መምህር ገለጹ።
Next article❝የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ ጉዳይ በአማራ ክልል የተወረሩ አካባቢዎችንና ወገኖቻችን ከጠላት ነፃ ማድረግ ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ