የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓትን ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።

222

መስከረም 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር) ነገ በሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኅዳር 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።

በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ምስረታ ላይ ለመታደም የተለያዩ እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀምረዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበአማራ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመመከት የተጀመሩ ሁሉ አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ።
Next articleቤት አልባ ባለቤቶች!