
መስከረም 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል አዲሱ ካቢኔ በጸጥታ ጉዳይ ላይ በመወያዬት የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሂዷል።
የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አሁን ካለንበት የህልውና ስጋት አኳያ ካቢኔው ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው የጸጥታ ጉዳይን ነው።
ውይይቱም የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መስራች ጉባኤ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ወደ ተፈጻሚነት ለማሸጋገር ያለመ ነው ብለዋል።
መድረኩ የተሰጠንን ሕዝባዊ የጋራ ኃላፊነት በአግባቡ ለመውጣት በመልካም ጅምርነቱም የሚወሰድ መሆኑን ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።
በአማራ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመመከት የተጀመሩ ሁሉ አቀፍ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።
ካቤነው እና አዲሱ መንግሥታቸው ድርብ ኃላፊነቶችን ለመወጣት ቁርጠኛ ነው ሲሉ ዶክተር ይልቃል ማስታወቃቸውን ከርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m