
ደሴ፡ መስከረም 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች 650 ሺህ ብር የሚገመት የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአሸባሪው የትህነግ ወረራ ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የተጠለሉ ወገኖችን ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተመልክተው ነበር፡፡
ፕሬዚዳንቷ በቦታዉ ተገኝተዉ ተፈናቃይ ወገኖች ያጋጠማቸውን ችግር በማየት የነበረዉን ክፍተት ለመሙላት በገቡት ቃል መሠረት እንደተፈጸመ ድጋፉን በስፍራው ተገኝተው ያስረከቡት የፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት አስተዳደር እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ዮናስ ተረፈ ገልጸዋል፡፡
የፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤቱ ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ድጋፉ መደረጉንም አንስተዋል፡፡
ተፈናቃይ ወገኖችን ለመደገፍ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡
ድጋፋን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ መሳይ ማሩ ለተደረገዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዉ የሚደረገዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ማህሌት ተፈራ-ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ