
መስከረም 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዋሽ ቢሾላ ማሰልጠኛ ማእከል በኹለተኛ ዙር ለከተቱት ምልምል ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የሥራ መመሪያ የሰጡት የአዋሽ ቢሾላ እና የቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች የበላይ አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ዲሪባ መኮንን ናቸው።
ጀነራል መኮንኑ በሰጡት የሥራ መመሪያቸው ፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በስልጣን በቆየባቸው ጊዜያት በሕዝቦች ላይ ግፍና በደል እየፈጸመ ቆይቷል ፡፡ አሁንም የሕዝብና የመንግሥት ንብረትን ከመዝረፍና ሕጻናትን ከመድፈር አልፎ በእንስሳት ላይም ሳይቀር ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በመፈጸም ላይ ይገኛል ብለዋል።
“መንግሥት የአሸባሪ ቡድኑን እኩይ ተግባር ለማክሸፍና ሕግን ለማስከበር እየወሰደ ባለው ዘመቻ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀላቀል የሚጠብቅባችሁን ለማበርከት ስለመጣችሁ ልባዊ አክብሮቴን አቀርብላችዋለሁ” ነው ያሉት ፡፡



የአዋሽ ቢሾላ ማሰልጠኛ ማእከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል ተረፈ ጩሪሶ በበኩላቸው በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ቆይታችሁ የሚሰጣችሁን ወታደራዊ ስልጠና በእልህና ሞራል በመሰልጠን የመጣችሁበትን ሀገር የማዳን ዓላማ ከግብ ማድረስ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።
በመክፈቻ መርኃ ግብሩ ላይ በሥራ አፈጻጻመቸው ውጤት ላስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊቱ አባላት በሌተናል ጀነራል ድሪባ መኮንን ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ሥርዓት መከናወኑን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ