
አዲስ አበባ፡ መስከረም 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩና ከተሰማሩበት ዓላማ ውጪ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዳ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ሰባት የውጭ ዜጋ ሠራተኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ ሕጋዊነትን ለማስፈን የተወሰነ፣ ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡
በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ 7 ሠራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ ከሀገር እንዲወጡ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘዙን ተከትሎ ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ግለሰቦቹ ከሀገር እንዲወጡ የታዘዙት ከተሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ሲንቀሳቀሱ እና በሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው።
እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፣ ማንኛውም ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋምም ሆነ ግለሰቦች ሲገቡ ፈቃድ አላቸው፤ የሚሠሩትም በፈቃድ ነው።
የትኛውም ተቋም እና ግለሰብ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከተገኙ ተግባሩ ሕገ-ወጥ ነው፤ ከሀገር እንዲወጡ በታዘዙት ግለሰቦች የሆነውም ይኸው ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና፡፡ ኢብኮ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m