
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ አንስተዋል።
በአሸባሪው ቡድን ወረራ ስር የሚገኙ ዜጎች የሕክምና አገልግሎት በማጣት በሕመም እየተሰቃዩና ሕይወታቸው እያለፈ እንደሚገኝ የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል።
መንግሥት በአፋጣኝ ወረራ የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች ነፃ እንዲያወጣም አሳስበዋል።
የአማራ ሕዝብ በታሪኩ ክህደት ተፈጽሞበታል፣ የሀገር ውስጥ ባንዳዎች ከፍተኛ ውድመት እያደረሱበት ነው፤ ወራሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ይህም እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል።
ጠላት በፍጥነት መውጣት ካልቻለ ችግሩ የበለጠ የከፋ ይሆናል፤ የፌዴራልና የክልል ጸጥታ ኀይል በቅንጅት የተጠናከረ ርምጃ መውሰድ አለበት ነው ያሉት።
ከውይይቱ በኋላም ምክር ቤቱ የውሳኔ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ