
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ቢጄአይ ኢትዮጵያ በአሸባሪው የትህነግ ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። በድጋፉም 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ከሠራተኞቹ በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡ በቀሪ አንድ ሚሊዮን ብር የብርድ ልብስ ድጋፍ ያደረጉት ደግሞ የሉሚኒየስ ትሬዲንግ ባለቤት እና የቢጂአይ አይ ኢትዮጵያ ወኪል አከፋፋይ የሆኑት አቶ ዝናቤ ሞላ ናቸው።
ከጦርነት በኋላም መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ከማኅበረሰቡ ጎን ድርጅቱ እንደሚቆም ገልጸዋል።
በኮምቦልቻና በደሴ ከ350 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች እንደሚገኙ ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አመላክቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ13 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት በመጠለያ እንደሚገኙ ገልጸዋል። እስከ ባለፈው ሳምንት ከ253 ሺህ የሚሆኑት ድጋፍ ተደርጓል። 96 ሺህ የሚሆኑት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ተጠቅሷል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ