
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ በውሎው የሚከተሉትን መርሃ ግብሮች ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል:-
-የምክር ቤት አባላት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ
-የአፈ-ጉባዔ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ይካሄዳል
-የአፈ-ጉባዔ እና የምክትል አፈ-ጉባዔ ምርጫ ይከናወናል
-የአፈ-ጉባዔ እና የምክትል አፈ-ጉባዔ ቃለ-መሃላ ይፈጸማል
-የነባር አፈ-ጉባዔ ከአዲስ አፈ-ጉባዔ ርክክብ ይካሄዳል፣አፈ-ጉባዔ ንግግር ያደርጋሉ
-ቋሚ ኮሚቴዎች ይሰየማሉ
-ቋሚ ኮሚቴዎች ቃለመሃላ ይፈጽማሉ
-የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ይሰይማሉ
-የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ
-የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ንግግር ያደርጋሉ
-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የካቢኔ ሹመቶች ቀርበው በምክር ቤቱ ይጸድቃሉ
-ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ
-በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የተሾሙ ቃለ-መሃላ ይፈጽማሉ
-የካቢኔ አባላት ቃለ-መሃላ ይፈጽማሉ
-የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የዳኞች አስተዳድር ጉባዔ የምክር ቤት ወኪሎች ይሰየማሉ።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ