
መስከረም 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደኅንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው
ተቋም መሆኑ ይታወቃል።
አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ እንዳመለከተው ለዜጎች ሰላም መረጋገጥ እንዲሁም የቁልፍ መሰረት ልማቶችን ደኅንነት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመጠበቅና ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ሕጋዊ ፈቃድ ለቀረጻ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል አሳስቧል፡፡
አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ሕዝባዊ ኹነቶች ላይ ለቀረጻ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ መሆኑን ያመለከተው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ፤ ጉዳዩ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከሕገ ወጥ
ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አስታውቋል፡፡
ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም
ግለሰብ በሕግ እንደሚጠየቅ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m