
ደሴ፡ መስከረም 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከዛሬ 21 ዓመት በፊት የተቋቋመው የቤዛ ፖስትሪቲ የልማት ድርጅት የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
የቤዛ ፖስትሪቲ የልማት ድርጅት በአጣየና አካባቢው ዘላቂ ሰላም መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በኮምቦልቻ ከተማ እየመከረ ነው።
ወጣት ኢብራሂም ሁሴን የከሚሴ ከተማ ነዋሪ ነው። በውይይቱ ላይ እንዳነሳው የአጣየ እና አካባቢዋ ማኅበረሰብ ጥሩውንም ክፉውንም ጊዜ በጋራ አሳልፈዋል።
የፖለቲካ ቁማርተኞች ሁለት ወንድማማች ሕዝቦችን ለማጋጨት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል ነው ያለው።
የአጣየ ከተማ ነዋሪ ወጣት አውራሪስ መሰለ በበኩሉ በደረሰው ጉዳት ምን ያክል ዋጋ እንደተከፈለ ታይቷል ብሏል። ወጣቶች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሀገራቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል።
የቤዛ ፖስትሪቲ የልማት ድርጅት ዳሬክተር ሰይድ አሕመድ በተለይ በአካባቢው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሠራ ገልጸዋል። ለዚህም ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ሥራ ተገብቷል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ-ከኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ