በአይከል ከተማ የአማራና የቅማንት ወንደማማችነትን የሚያጠናክር ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነዉ።

210

መስከረም 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቅማንት ሕዝብ ሀገርን የሚያፈርስ ዓላማ ካለው የአሸባሪ ቡድን ጋር ሕብረት እንደሌለው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ሀገርን ለአደጋ ያጋለጡ ከሀዲወችን እንደሚያወግዙም ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የአማራ እና የቅማንት ሕዝብን አንድነት የሚለይ ሊኖር አይችልም ያሉት ሰልፈኞቹ ‟እኛ ልጆቿ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም” ብለዋል፡፡

በሰልፉ ላይ የአይከል ከተማ አስተዳደር፣የጭልጋ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች፣ ነዋሪዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡- አዲስ ዓለማየሁ – ከአይከል

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleተሰናባቹ የአማራ ክልል ምክር ቤት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ ገለጹ፡፡
Next articleየቤዛ ፖስትሪቲ የልማት ድርጅት በአጣየና አካባቢው ዘላቂ ሰላም መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በኮምቦልቻ ከተማ እየመከረ ነው።