ተሰናባቹ የአማራ ክልል ምክር ቤት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ ገለጹ፡፡

522

ባሕር ዳር: መስከረም 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣7ኛ ዓመት 18ኛ መጨረሻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ምክንያት ጉባኤው ዘግይቶ የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሽብርተኛው ትህነግ ጠብ ጫሪነት ክልሉ ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤዋ የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ወረራ ዜጎች ለሞትና መፈናቀል መዳረጋቸውንም አንስተዋል።

ምክር ቤት ባለፉት ዓመታት የክትትልና የቁጥጥር ሥራን ዋነኛው ግብ በማድረግ በክልሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጡ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን በደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ፣ የአብሮነት እሴት እንዲጎለብት፣ ከጎረቤት ክልሎች ልምድ በመውሰድም የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

ወይዘሮ ወርቀሰሙ ቀጣይ የሚመሠረተው መንግሥት አሸባሪው ትህነግ የከፈተውን ወረራ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን መመከትና ኢትዮጵያን የማትደፈር ሀገር ለማድረግ እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረግ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል ነው ያሉት። ተፈናቃዮችን ማቋቋም፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነት መፍትሔ ማበጀት ሌሎች ዋና ተግባራት መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መካሄዱን በአድናቆት ያነሱት ዋና አፈጉባኤዋ አሁንም ተገደን የገባንበት ጦርነት በአጭሩ እንዲጠናቀቅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በምርጫ ዘመኑ ጥሩ አገልግሎት ለሰጡ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ጉባኤው 80 ቢሊየን 104 ሚሊየን 669 ሺህ 397 ብር ለ2014 የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀት አቅርቧል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአዲስ የሚመሰረተው መንግሥት የሀገርን ሰላም ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርግ እንደሚገባ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next articleበአይከል ከተማ የአማራና የቅማንት ወንደማማችነትን የሚያጠናክር ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነዉ።