
ባሕርዳር፡ መስከረም 17/2014 (አሚኮ) በኢትዮጵያ አየር ኃይል የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑና የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ለነበራቸው ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማዕረግ ማልበስ ሥነ ስርዓት ተከናወኗል።
የኢትዮጵያ አየር ኀይል ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ይልማ መረዳሳ አየር ኃይል ከተቋማዊ ሪፎርሙ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመጥን ተቋም ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በሕግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻውም አስደናቂ ገድሎችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት አለን ያሉት ዋና አዛዡ ፣ በቀጣይም ሀገራችንን የሚዳፈር ማንኛውም ኃይል ላይ አስተማሪ ቅጣት በመስጠት ተልዕኳችንን በብቃት ለመወጣት የዕለቱ ተሿሚዎች የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኀይል ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ብ/ጄ ይታያል ገላው በበኩላቸው፣ በውስጥና በውጭ ኃይሎች የተደቀኑብንን ፈተናዎች በፅናት በማለፍ በአዲስ ዓመት የሽብርተኛውን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ሕዝባችንን ደጀን አድረገን የህልውና ዘመቻ የምናደርግበት ወቅት በመሆኑ የማዕረግ ሹመቱ ልዩ ነው ብለዋል።
መረጃው የመከላከያ ሠራዊት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ