ኢትዮጵያዊትና ኤርትራዊ ሙሽሮች 10 ሺህ ዶላር የሰርግ ወጪያቸውን ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ለገሱ።

374
መስከረም 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያዊቷ ሙሽሪት ብዙዓለም ተገኔ እና ኤርትራዊው ሙሽራ ዳንኤል ባህታ 10 ሺህ ዶላር የሰርግ ወጪያቸውን በኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ወገኖች አበርክተዋል፡፡
ሙሽሮቹ ድጋፉን ያደረጉት ❝ወገኖቻችንን እንርዳ❞ በሚል በፐርዝ ምዕራብ አውስትራሊያ በተካሄደ ልዩ የመስቀል በዓል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
ሙሽሪት ብዙዓለም ተገኔ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ❝ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለችበት ወቅት የምንደርስላት እኛ ነን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በቃሽ እንዲላትና ጋብቻንንም እንዲባርክልን በፀሎታችሁ አስቡን❞ ብላለች፡፡
ሙሽራው ዳንኤል ባህታ በበኩሉ ❝ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አንድ ነን፤ ችግሩ የጋራችን ነው❞ ብሏል። ኤስቢኤስ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየላቀ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ።
Next article“ኢትዮጵያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት አለን” የኢትዮጵያ አየር ኀይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ይልማ መርዳሳ