
መስከረም 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ።
የማእረግ አሰጣጥ መርኃ ግብሩም የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት ተከናውኗል።
የማእረግ እድገቱ የተሰጣቸው የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1936 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማስከበርና ለሀገሩ ሉዓላዊነት በመቆም የገዘፈ ታሪክ ያለው ተቋም መሆኑ ይታወቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ