
መስከረም 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሰተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተፈናቃዮቹ በሚገኙበት እብናት ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ በመገኘት ድጋፉን አስረክቧል።
በእብናት ከተማ የተደረገው ድጋፍ ግማሹ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች እንዲደርስ የታሰበ ቢሆንም በደቡብ ወሎ ድጋፉን ከሚያስተባብሩ አካላት ጋር በነበረው ውይይት በእብናት እየጨመረ ከመጣው እና ካለው ተፈናቃይ ቁጥር አንፃር ለዋግና አካባቢው ተፈናቃይ ወገኖች እንዲደርስ መወሰኑን ነው ዩኒቨርሲቲው የገለጸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው እና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ከዚህ ቀደም በደባርቅ ግንባር እና በጋይንት ግንባር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሰለሞን ፋንታው ገልጸዋል።
መረጃው የተገኘው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ