
ባሕር ዳር፡ መስከረም 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአጣዬ ከተማና አካባቢው ተከስቶ በነበረው የሰላም እጦት በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች ደርሰዋል።
ከዚህ ችግር ማግስት አካባቢው መልሶ እንዲረጋጋና ዜጎችም እንዲቋቋሙ እየተሠራ ነው።
እየሩሳሌም የሕፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት ያዘጋጀው ውይይት በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን የመገንባት ዓላማ ይዞ በአጣዬ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አገኘሁ መክቴ አሁን በከተማዋ እየመጣ ያለውን ሰላም ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ የፈጸመውን ወረራ አስከፊነት ከኛ በላይ የሚረዳ የለም ያሉት ከንቲባው ወረራውን በአንድነት መክተን ሰላማችንን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
በአካባቢው የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ተወካይ ኮሎኔል ተከተል ልኬን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ አካላት እና በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የውይይቱ ተሳታፊ ሆነዋል። ውይይቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣም ያግዛል ተብሏል።
ዘጋቢ፡-ኤልያስ ፈጠነ -ከአጣዬ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ