በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን የተጎዱ እናት 55 ሺህ ብር ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡

335
መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ዘቢጥ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እማሆይ ሲሳይ ዋጋው አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በቤታቸው ውስጥ የሚገኘውን ጥሪት አሟጥጦ በመውሰዱ ችግር ላይ መውደቃቸውን አሚኮ ጳጉሜን 5/2013 ዓ.ም መዘገቡ ይታወሳል። እማሆይ ሲሳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀው ነበር።
በመሆኑም ይህን ዜና የተመለከተው በአሜሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ደሳለኝ አበራ ለእማሆይ ሲሳይ የ55 ሺህ ብር ድጋፍ አበርክቶላቸዋል። እማሆይ ሲሳይ ለተበረከተላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ አመስግነዋል።
“ከችግሬ እንድወጣ ይህን ገንዘብ ያበረከተልኝን ቅን አሳቢ እግዚአብሔር እንጀራውን ይባርክለት! የዘመን መለወጫን በችግር ባሳልፈውም አሁን የመስቀል በዓልን በደስታ እንዳሳልፍ አድርጎኛል። ዓዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ የሚጠፉበት እንዲሆንም ተግቼ እጸልያለሁ” ብለዋል። ድጋፉን እንዲያገኙ ላስተባበሩላቸው ሁሉ አመስግነዋል።
ባለ ሀብቶች እንደ እሳቸው ላሉ አቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ ይህን ክፉ ጊዜ እንዲሻገሩ ሊረዷቸው እንደሚገባም እማሆይ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ-ከደብረ ዘቢጥ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ከተለያዩ የሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ የተጠለሉ ወገኖችን ተመለከቱ፡፡
Next article“ውድ ሕይዎቱን ለሀገሩ የሚሰጥ ሁሉ ክቡር ነው” ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ