
ደባርቅ: መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሀብቱ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል። ባለሀብቱ ካደረጉት የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ለሠራዊቱና ለተፈናቃዮች የ1 ሚሊዮን ብር የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የግንባሩ የመከላከያ ሠራዊት የሥራ ኀላፊዎች፣ የደባርቅ ከተማ ባለሀብቶችና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡
ባለሀብቱ ከድጋፉ በተጨማሪ በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ምክንያት ከተለያዩ የሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ መጠለያ ውስጥ የተጠለሉ ወገኖችን ተመልክተዋል፡፡
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በአሁኑ ወቅት ለአማራ ሕዝብ ጠላት የሆነውን አሸባሪው የትህነግ ቡድንን ለማጥፋት ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነት መታገል ይገባል ነው ያሉት፡፡
በግንባሩ ለተገኘው ድል የዞኑን ሕዝብና የሠራዊቱን ጀግንነት አድንቀዋል፡፡
በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ባለሀብቱ ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ:- አድኖ ማርቆስ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ