ሽብርተኛው ትህነግ ለሥልጣን መጠቀሚያ ሲል በትግራይ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው መከራ ሊያበቃ ይገባል ስትል ታዋቂዋ ኢትዮ አሜሪካዊት ትግራዋይ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ገለጸች፡፡

814
መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሁኑ ወቅት በሲቢኤስ የዜና መረጃ መረብ በመሥራት ላይ የምትገኘው እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛ ልምድ ያላት ታዋቂዋ ኢትዮ አሜሪካዊት ትግራዋይ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ አሸባሪው ትህነግ የትግራይን ሕዝብ ለስልጣን ጥቅሙ ብሎ እየተጠቀመበት እንደሆነ በትዊተር ገጿ አመላክታለች።
ሽብርተኛው ትህነግ የፌዴራል መንግሥት እያደረገ ያለውን መልካም ተግባር ጥላሸት ለመቀባት ሲል ሰብዓዊ ድጋፍ ለትግራይ ሕዝብ እንዳይደርስ እያደረገ መሆኑን ተችታለች፡፡ አሸባሪው ትህነግ ለሥልጣኑ ሲል በትግራይ ሕዝብ ላይ መከራ እያደረሰበት መሆኑን ነው የገለጸችው።
ሔርሜላ በቅርቡ በለቀቀቻቸው ጽሑፎች ❝የኢትዮጵያ መንግሥት በተናጠል ያወጀውን ተኩስ አቁም አሸባሪው ትህነግ ለምን ጣሰ? ወደ አማራና አፋር ክልሎችስ ወረራ በማካሄድ ንጹሐንን ለመግደልና ውድመቶችን ለመፈጸም ለምን ፈለገ?” ስትል ጠይቃለች።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ወደ ትግራይ የእርዳታ እህል ጭነው ከተላኩት 466 ተሽከርካሪዎች የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው ያለውን ሪፖርት አጽንዖት በመስጠት የሽብር ቡድኑ በትግራይ ሕዝብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ግፍም አውግዛለች።
ጋዜጠኛዋ ❝እርዳታ ጭነው የገቡ መኪኖች አለመመለስ ለምን ሆነ? ይህ ለሕዝቡ እርዳታው እንዳይሰራጭ አያደርግም ወይ?❞ ስትል መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎችን አንስታለች፡፡
የሽብር ቡድኑን በጭፍን የሚደግፉ ሁሉ ሊያስቡበት እና ድጋፉ ለምንድነው የሚውለው የሚለውን መጠየቅ እንዳለባቸው ገልጻለች፡፡
ወቅቱ በውጭ የምንገኝ ደጋፊዎች ቆም ብለን ራሳችንን የምናይበትና ከጭፍን ድጋፍ ወጥተን መፍትሔ የምናመጣበት ጊዜ ሊሆን ይገባል ስትል ነው ያመለከተችው።
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleባለሀብቱ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ ።
Next articleባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ከተለያዩ የሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ የተጠለሉ ወገኖችን ተመለከቱ፡፡