ባለሀብቱ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ ።

432
ደባርቅ: መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሀብቱ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ባለሀብቱ በወሎና በአፋር ግንባር ለሠራዊቱና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የስሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ደብረወርቅ ይግዛው አሸባሪው ትህነግ ዋናው ዓላማው የአማራን ሕዝብ ቅስም በመስበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ መምጣቱን ገልጸዋል።
የስሜን ጎንደር ሕዝብ ከወገን ጦር ጋር በመሆን ተስፋ እንዲቆርጥና እንዲደመሰስ አድርጓል ብለዋል። አሸባሪው ቡድን ዓላማው ሀገርን መምራት ሳይሆን የማፍረስ ነው ያሉት ምክትል አስተዳዳሪዋ በዞኑ ዜጎችን ጨፍጭፏል፣ ሀብትና ንብረት ዘርፏል፣ አውድሟል ነው ያሉት።
ባለሀብቱ ወርቁ አይተነው የአካባቢው ማኅበረሰብ ጠላትን የደመሰሰበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል። መተባበር እና አንድ መሆን ይገባል ነው ያሉት። ሁሉም ሰው ጦርነቱ ወደ አለበት ቦታ መትመም አለበት ብለዋል። አንድ ለአምስት ሆነው ከመጡ እኛ አንድ ለ20 ሆነን መቅረብ መቻል አለብንም ነው ያሉት።
የተዛባ አስተሳሰብ የሚያስቡ ሰዎችም ማቆም መቻል አለባቸውም ብለዋል። ሁሉም ሰው በአንድነት የጋራን ጠላት ማጥፋት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ጋር በመቆም ሽብርተኛው ትህነግን ማጥፋት ይገባልም ብለዋል።
ኢትዮጵያን የካዱ ባንዳዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
አንድ መሆን ከተቻለ በጥቂት ቀናት ጠላትን ማጥፋት እንደሚቻልም ነው የተናገሩት።
የክልሉ ባለሀብት የተለያየ ተልዕኮ በመውሰድ እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ከነጋዴዎች አንድ ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንም ጠቁመዋል። ሁልጊዜም ከጎናችሁ አለን ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለተፈናቀሉ ወገኖች 500 ሺህ የሚገመት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleሽብርተኛው ትህነግ ለሥልጣን መጠቀሚያ ሲል በትግራይ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው መከራ ሊያበቃ ይገባል ስትል ታዋቂዋ ኢትዮ አሜሪካዊት ትግራዋይ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ገለጸች፡፡