የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

165
ደባርቅ: መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የሕልውና ዘመቻው ዋና አስተባባሪ አበባው አደራው አሸባሪው ትህነግ በግልፅ ወረራ ጥቃት ፈፅሟል፣ ገድሏል፣ ዜጎችን አፈናቅሏል፣ ሀብትና ንብረት አውድሟል ነው ያሉት።
ዋና አስተዳዳሪው ወራሪውን ለሚፋለመው የወገን ጦር በሎጅስቲክስ ማጠናከር አለብን በማለት ሀብት ማሰባሰባቸውን ነው የተናገሩት። ወረዳው በተለያዩ ግንባሮች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
የአሁኑ ድጋፍ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ለወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የጠቆሙት። የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ነውም ተብሏል። በድጋፉም 200 ኩንታል ደረቅ ሬሽን፣ 102 ፍየል እና ሁለት ሰንጋ ተበርክቷል፡፡
ሁሉም አካል ለተፈናቃዮች እና ለወገን ጦር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ሠራዊቱን በጎደለው ሁሉ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ድጋፉን የተቀበሉት ከምዕራብ እዝ ኃላፊዎች አንዱ የሆኑት በሕዝቡ የሚደረገው ድጋፍ ለሠራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖታል ነው ያሉት። ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል ሕዝቡ የሚጠብቀውን ለማሳካት በድል እየገሰገሰ ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
Next articleበአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለተፈናቀሉ ወገኖች 500 ሺህ የሚገመት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡