ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

315
ደሴ: መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመሆን ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የምግብ፣ የአልባሳትና ሌሎችም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ነው ድጋፍ የተደረገው፡፡
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተፈናቃዮች ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ ድጋፍ ማደረጉን ገልፆ፣ ለሰዎች ለሰዎች ድርጅትም ምስጋና አቅርቧል፡፡
ተፈናቃዮችን በመደገፍ ረገድ በቀጣይም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሳምንት በፊት በኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ – ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article”ሽብርተኛው ትህነግ ሦስት ነገሮችን ገድሏል – ሰውን፣ እንስሳትን እና እፅዋትን” ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
Next articleየደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦርና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ።