
ባሕር ዳር፡ መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
ሁለቴ ሞት የለም ሞት አንድ ጊዜ ነው፣
የገባውን ጠላት ገድለህ አሸንፈው፣
ጀግንነት ውርስህ ነው አሳየው ክንድህን፣
አሸብርቀህ ፃፈው የአባት አደራህን።
ጠላት እንደሆነ ያው ጠላት ነው። ከርሞም ወዳጅ አይሆንም። ምሱን ሰጥተው ካላጠፉት ገድለው ካልቀበሩት ረፍት አይሰጥም። የአባት አደራችን በጀግንነት መፋለም ነው። የተፃፈው ታሪካችን ማሸነፍ ብቻ ነው። እኛ የአሸናፊዎች አባቶቻችን ልጆች ነን። የዛሬውም ልማዳችን ይሔው ነው። ጦርነትም ቢሆን ሠርጋችን ነው። ጠላት እንዳበደ ውሻ ከሆነ ውሎ አድሯል። በዛም በዚህም ቢነካክሰንም ሞትና ቁስለኛ ሆኖ በየጥሻው መውደቁን ቀጥሏል።
በተለያዩ ግንባሮች የቅርቡን ድል ይዘን እስከመጨረሻው የሠይጣን ውላጁን ትህነግን እንቀብረዋለን፤ እንጂ ሌላ ምርጫ የለንም። በጋይንት የመጣው ጠላት የጀግናውን መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ብርቱ ክንድ ሊቋቋም አልቻለም።
በወሎ ግንባር ያለ የሌለ ኃይሉን አጓጉዞ የመጣው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የጀግኖቻችንን የእሳት ክንድ ማምለጥ ባለመቻሉ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እዛው ቀርቷል።
በሰሜን ጎንደርም የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ወደ ዳባት በአራት አቅጣጫዎች የመጣው ጠላት በገባበት ቀርቷል። ይህንን የዳባት ድል በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሽብርተኛው ትህነግ እየደረሠበት ያለው ሰብዓዊ ኪሳራ የትግራይን እናቶች የወላድ መካን ያደረገ ነው ብለውታል። የተመለከቱት የጠላት አስከሬን ብዛት ነው ይህንን እንዲሉ ያስገደዳቸው።
ሌላም ተናግረዋል። ስለ ሽብርተኛው ትህነግ የቀቢፀ ተስፋ ተግባር። በየትም ሀገር እና ታሪክ ጦርነት የገጠመ አካል የሚገድለው የሚዋጋውን ጠላቴ የሚለውን ወታደር ነው ብለዋል ዲያቆን ዳንኤል። ”ሽብርተኛው ትህነግ ግን ሦስት ነገሮችን ገድሏል – ሰውን፣ እንስሳትን እና እፅዋትን” ነው ያሉት፡፡ እውነት ነው ተሸናፊው ሽብርተኛው ትህነግ በየደረሠበት እያደረገ ያለው ይሔንኑ ነው። ሽብርተኛው ትህነግ ይህንን እያደረገ የሚገኘው እየተሸነፈ በመሆኑ ተስፋ በመቁረጡ ነው።
በሰሜን ወሎ እና በዋግኽምራ አካባቢዎችም የማይቀርለትን ሽንፈትም እየጠበቀ ነው።
ብዙ እንዳያጠፋ ጠላት ውሎ ሲያድር፣
ቅበረው ባለበት አትንፈገው አፈር፤
መጥፊያው ቢደርስ ነው የወረረው ሀገር።
በሀብተጊዮርጊስ አበይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ