❝አባቶቻችን ከሀገር ውስጥ ባንዳና ከውጭ ጠላት ጠብቀው ያቆዩንን ሀገር በጽናት እና በአንድነት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ኀላፊነት ነው❞ የቀድሞው ጦር ሠራዊት አባል ብርጋዴር ጄነራል ካሳዬ ጨመዳ

266

ጎንደር፡ መስከረም 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሸን ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውጭ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን ለማጥፋት ኢትዮጵያውያን በአራቱም ማዕዘን ሁሉንአቀፍ የትግል እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

❝አባቶቻችን ከሀገር ውስጥ ባንዳና ከውጭ ጠላት ጠብቀው ያቆዩንን ሀገር በጽናት እና በአንድነት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ወቅቱ የሚጠይቀው ኀላፊነት ነው❞ ብለዋል።

የሀገር ዳር ድንበር ጠባቂ እና ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ያለውን የመከላከያ ሠራዊትን በሰው ኀይልና በቁሳቁስ ማጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ አሸባሪው የትህነግ ቡድን እንዲከስም ሕዝቡ ወደ ግንባር በመዝመት እያሳዬ ያለውን ደጀንነት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

❝አሸባሪው የትህነግ ቡድን የከፈተው ጦርነትና ወረራ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነት መታገል አለባቸው❞ ነው ያሉት።

መስከረም 24/2014 ዓ.ም የሚመሰረተው አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕግና ሥርዓትን በማስከበር፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራትን በማካተት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እድገት እንዲሠራም ጠይቀዋል።

ጠንካራ ተቋማት እንዲገነቡም የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባውም ብርጋዴየር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ጳውሎስ አየለ – ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበአሸባሪው ትህነግ አመራሮች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ጎራ ለይተው የተሰለፉ ታጣቂዎች እርስ በእርስ መገዳደላቸው ተገለጸ።
Next articleበኢትዮጵያ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት መንግስት በላቀ አጋርነት ከተመድ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።