❝ጠላት ካልጠፋ በስተቀር ከትግል ወደኋላ አንመለስም፤ ለሀገርና ለወገን ሰላም ስንል በትግላችን እንቀጥላለን❞ የዛሪማ ሚሊሻዎች

219
ደባርቅ: መስከረም 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በስሜን ጎንደር ዞን የገባው የትግራይ ወራሪ ቡድን አብዛኛው ተቀጥቅጦ አፈር ለብሷል። የቀረውም ወደ ኋላ ተመልሷል። ነገር ግን አሁንም በደል እየፈፀመባቸው የሚገኙ የስሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች አሉ። አሸባሪው ቡድን የወረራቸውን ለማስለቀቅ እና ግብዓተ መሬቱን ለመፈጸም የወገን ጦር በተጠንቀቅ ላይ ነው።
በዛሪማ ያገኘናቸው የዛሪማ ሚሊሻዎች ጠላትን በቶሎ ድባቅ መትተው ከአካባቢው ለመንቀል መቸኮላቸውን ተናግረዋል።
የዛሪማ ሚሊሻ ዓለሙ ወርቄ ትህነግ የዛሪማና አካባቢውን ሕዝብ ሲጨቁን የኖረ ቡድን መሆኑን ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑን ለማጥፋት መነሳታቸውንም ተናግረዋል። ወራሪውን ቡድን ድባቅ መምታታቸውን የገለጹት ሚሊሻው የቀሩትን ለመቅበር ዝግጁ ነን ብለዋል።
❝ጠላት ካልጠፋ በስተቀር ከትግል ወደኋላ አንመለስም፣ ለሀገርና ለወገን ሰላም ስንል በትግላችን እንቀጥላለን❞ ነው ያሉት።
በአዲቋራ ሚካኤል ላይ በነበረው ውጊያ ከአንድ ጓደኛቸው ጋር በመሆን አራት የጠላትን ቡድን መማረካቸውን ገልጸዋል። በነበሩበት ግንባር ከጠላት ልቀው ድል ማስመዝገባቸውንም ተናግረዋል። የቀረውን ጠላትን ድባቅ ለመምታት ዝግጁ ነንም ብለዋል። ❝ያልቃሉ እንጂ በፍፁም አያሸንፉም፤ አማራን የሚያሸንፈው የለም❞ ነው ያሉት።
በነብራ፣ በጨው በርና በበር ማርያም የሚኖሩ ንጹሐን አማራዎች አሁንም በደል እየደረሰባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ መረጃ ታቀብላላችሁ በሚል ወደ ዛሪማ ገበያ እንዳይመጡ መከልከላቸውንም ገልጸዋል።
ሌላኛው ሚሊሻ እያዩ ፀጋ በገቡበት ቦታ ሁሉ አስከሬናቸው እንጂ ሕይወታቸው አልተመለሰም ብለዋል። ❝በጣም ነው የተጨፈጨፉት፤ አሁንም ጊዜ ልንሰጣቸው አይገባም ነው❞ ያሉት።
አርሶአደሩን እያንገላቱት ነው፤ ከአካባቢው በፍጥነት መውጣት አለባቸውም ብለዋል።
አዝመራው ለአጨዳ ከመድረሱ በፊት ከአካባቢው መነቀል አለባቸው፤ የአዝመራውን ሲዘርፉ የቆዩ ወራሪዎች አሁንም አዝመራው ሲደርስ ለሌላ ዘረፋ እንዳይሰማሩ አስቀድሞ ዋጋቸውን መስጠት ይገባልም ነው ያሉት።
ወራሪው ቡድን ከአማራ ምድር በፍጥነት ተጠራርጎ መውጣት እንደሚገባውም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገዘብ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።
Next articleሀገርን ከውስጥ ባንዳ እና ከውጭ ጠላት ለመጠበቅ የተጣለባቸውን ኀላፊነት በሚገባ እንደሚወጡ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉ ወጣቶች ገለጹ፡፡