በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገዘብ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።

171
ባሕር ዳር፡ መስከረም 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአየርላንድ የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስትር ስምዖን ኮቨኒ ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል።
በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል አሸባሪው ትህነግ አጠናክሮ የቀጠለባቸውን እኩይ ጥፋት እና ጥቃቶችን ተከትሎ በመንግሥት በኩል በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ክሶች መነሻቸው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል ካለመረዳት የመነጨ ነው ብለዋል።
የአሸባሪው ትህነግ ጥፉት የወራት ዕድሜ መነፅር ብቻ የሚመዘን ሳይሆን ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ዜጎች ሞት ጀርባ ምክንያት የነበሩ አሸባሪዎችን ሲያደራጅ፣ ሲደግፍ እና ስምሪት ሲሰጥ እንደነበር በዝርዝር አብራርተዋል።
መንግስት በሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ እና የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚወስዳቸው ህጋዊ እርምጃዎች ዙሪያ ሚዛናዊነት በጎደለው አግባብ መረዳት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ነባራዊ እውነታ መሸሽ እንደሆነ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲሁም በሁሉም ወዳጅ ሀገራት እይታ ዘንድ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ግንዛቤ እንዲያዝ እንፈልጋለን ነው ያሉት አቶ ደመቀ።
መንግስት በኀላፊነት ስሜት የሚወስዳቸውን የሰላም አማራጮች እና ህጋዊ እርምጃዎች ተከትሎ ተደጋጋሚ ክሶች መቅረባቸውን ጠቁመዋል። በተደጋጋሚ የሚቀርቡት ክሶች ተቀባይነት የሌላቸው እና በሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጎዱ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
በመጨረሻም የአየርላንድ መንግሥት ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የሰጠውን ትኩረት በማድነቅ፤ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገዘብ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር አደረገ።
Next article❝ጠላት ካልጠፋ በስተቀር ከትግል ወደኋላ አንመለስም፤ ለሀገርና ለወገን ሰላም ስንል በትግላችን እንቀጥላለን❞ የዛሪማ ሚሊሻዎች