የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር አደረገ።

187
መስከረም 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ።
ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የሀገራችን ወቅታዊ የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ለውጦችን የተመለከቱ አጀንዳዎች እንደሚገኙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
የሚታዩ ክፍተቶችን፣ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው እና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ እንደ ሀገር መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት አቅጣጫዎችን እንዳስቀመጠም ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ዋና አስተባባሪ ጋር ተወያዩ።
Next articleበኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል በመገዘብ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።