
መስከረም 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ አሕመድ ቢን አሕመድ አሊ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በተመሳሳይ አቶ ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓኮሜ ሞቤሌት ቡቤያ ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ተነስተዋል።
በቅርቡ ጋቦን ወደ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቀጣይ አባል መሆኗን ተከትሎ ለአፍሪካውያንን ድምፅ በመሆን ሚናዋን እንደምትወጣ ዕምነታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።
የጸጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ትኩረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ