የዘንድሮው የመስቀል በዓል ሲከበር የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በማሰብ ሊሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለጸች፡፡

136
አዲስ አበባ፡ መስከረም 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የዘንድሮውን የመስቀል በዓል በስኬት ለማክበር ዝግጅት ማድረጓን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች፡፡
የዘንድሮው የመስቀል በዓል በአዲስ አበባ በድምቀት እንደሚከበር ቤተክርስቲያኗ የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ተናግረዋል፡፡ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በመስቀል አደባባይ ጎብኝዎችን በሚስብ መልኩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
በዓሉ ኢትዮጵያ ራሷን የምታስተዋውቅበት ሃይማኖታዊ በዓል ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ የኮሮና ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ በዓሉን ለማክበር የሚገኙ ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክረ ሀሳብ በመቀበል ርቀትን በመጠበቅ እና የአፍና አፍንጫ ጭምብል በመጠቀም ሊያከብር ይገባል ነው ያሉት፡፡
ሁሉም በዓሉን ሲያከብር የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በማሰብ አካባቢውንም ከጸጥታ ኀይሎች ጋር በመቀናጀት በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባም አብራርተዋል፡፡
የተፈናቀሉትን ለመደገፍ በቤተክህነቱ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡ በዓሉ በስኬት እንዲከናወንም ሁሉም ዜጋ ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ራሄል ደምሰው- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሁለት ዘረኞች ወግ
Next articleየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ብሔራዊ የደኅንነት ስጋቶችን በማስቀረት በኩል ስኬታማ ሥራዎች ማከናወኑን አስታወቀ።