የጎንደር ከተማ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ለህልውና ዘመቻው የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር እያካሄዱ ነው።

140
ጎንደር፡ መስከረም 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ በጎፈቃደኛ ወጣቶች እያካሄዱት ያለው የገቢ ማሰባሰብ ሥራ እስከ መጭው እሁድ የሚቆይ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡
መስከረም 10 የተጀመረው የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚውል ነው።
በጎ ፈቃደኛዋ ወጣት ትዕግስት ሲሳይ ገቢ የማሰባሰቡ ተግባር ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ለማሳተፍ ታስቦ እየተሠራ መሆኑን ተናግራለች።
ትናንት የበጎ ፍቃደኞች ቀን የተከበረ መሆኑን እና በእለቱ ከ20 ሽህ ብር በላይ መሰብሰቡን በጎ ፈቃደኛዋ ወጣት ትዕግስት ገልጻለች።
መርሃ ግብሩ ዛሬም ቀጥሎ የአሽከርካሪዎች ቀን ሲከበር በቀጣይ ረቡዕ የፋሲል ከነማ ቀን፣ ሐሙስ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀን፣ አርብ የጁምዕ እለት የእስልምና እምነት ተከታዮች ቀን ይከበራል።
ቅዳሜ የነጋዴዎች እና በባንክ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁኖ ቀኑ ሲታሰብ እሁድ የሰንበት ቀንን የክርስትና እምነት ተከታዮች ድጋፍ የሚያደርጉበት ቀን መሆኑን በጎ ፈቃደኛዋ ወጣት ትዕግስት ነግራናለች።
በእነዚህ ቀናት ሁሉም የቻለውን በማገዝ የተቸገረ ወገኑን አለሁ ሊል እንደሚገባ ትዕግስት አብራርታለች።
በበጎ ፈቃድ ሥራው የተሰማሩ ወጣቶች ሁሉም ሀገር ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት ሃብት ያለው በሃብቱ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ እንዲሁም በእውቀቱ መደገፍ አለበት ብለዋል።
ጉዳቱ በቀጣይ የእያንዳንዱን ቤት ከማንኳኳቱ በፊት ለተፈናቀሉ እና ግንባር ለሚዋደቁ የጸጥታ አባላት ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየህልውና ዘመቻዉ በሚጠይቀው መጠን በቂ ሃብት እየተሰበሰበ አለመሆኑን የአማራ ክልል ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
Next articleአሸባሪው የትህነግ ቡድን የፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጥናት በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽ ሊደረግ ነው።