አሸባሪው ትህነግ ከባድ መሳሪያ በመጠቀም በአንድ ቀን ከ600 በላይ ንጹሐንን እንደጨፈጨፈ ከቆቦ ከተማና ዙሪያዋ ተፈናቅለው በዞብል የተጠለሉ የዓይን እማኞች ገለጹ።

439

መስከረም 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማና ዙሪያዋ በሚኖሩ ወገኖች ላይ ግፍ ፈጽሟል፡፡ ከተማዋን ከወረረበት ጊዜ ጀምሮ የመንግሥት እና የግለሰብ ንብረት ዘርፏል ከተማዋን አውድሟል።

“የሽብር ቡድኑ አባላት ሴት ሕፃናትን ጭምር አስገድደው ለ6 ደፍረዋል፤ ከሴቶች ጆሮ ላይ የጆሮ ጌጥ ዘርፈዋል፤ ቀለበት ወስደዋል፤ የአንገት ሐብል ቀምተዋል፤ የሚፈልጉትን ልብስ አስወልቀው ለብሰዋል፤ ሰዓትና ሺርጥ ሰርቀዋል፤ የአርሶ አደሮችን ቤት ነዳጅ ተጠቅመው አቃጥለዋል” ብለዋል የዓይን እማኞቹ፡፡

የትህነግ የሽብር ቡድን በቆቦ ከተማና ዙሪያዋ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ የፈፀው ግፍ ሰላም የነሳቸው የከተማዋና ዙሪያዋ ወጣቶች ተደራጅተው በግንባር ተፋልመዋቸዋል፡፡ ሽብር መፍጠር እንጂ ፊት ለፊት መፋለም የማያውቁት የትህነግ አሸባሪ ቡድን አባላት የወጣቶቹን ጠንካራ ምት መቋቋም ሲሳናቸው ጳጉሜ 4/ 2013 ዓ.ም የቆቦ ከተማን ለቀው ፈርጥጠዋል፡፡

ይሁን እንጅ ከጎብዬና ሮቢት አካባቢዎቾ የነበረውን ወራሪ ኃይላቸውን በማቀናጀት ዲሽቃ፣ ብሬልና ዙ-23 የተሰኙ ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚፋለሟቸውን ወጣቶች በመበተን የቆቦ ከተማን በድጋሜ ከያዙ በኋላ ከ600 በላይ ንፁሐንን በገፍ ጨፍጭፈዋል ነው ያሉት የአይን እማኞች፡፡

በተለይ ወንዶችን የ11 ዓመት ሕጻን ሳይቀር ከየቤቱ እያደኑ ገድለዋል ነው ያሉት፡፡ የተገደሉ ወገኖች እንዳይቀበሩም በመከልከል በጅብ እንዲበሉ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

አማራ ጠልነታቸውን በግልጽ ለማሳዬት የማይፈፅሙት ግፍ የለም የሚሉት በዞብል አነስተኛ ከተማ የተጠለሉት የቆቦ ከተማና ዙሪያዋ ቀበሌ የአይን እማኞቹ ሕዝቡ በከፋ ችግር ውስጥ ስለሆነ መንግሥት አካባቢውን መልሶ እስከሚቆጣጠር ዓለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ሊደርሱ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሽብር ቡድኑ ላይ ፈጣን እርምጃ ካልተወሰደ የከፋ እልቂት ሊፈጸም ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፦አሊ ይመር -ከራያ ቆቦ ዞብል

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“እኔ በኢትዮጵያ ተስፋ አልቆርጥም” ክቡር ዶክተር ኦባንግ ሜቶ
Next articleየአሜሪካን መንግሥት ማእቀብ በመጣል የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝና ተንበርካኪ መንግሥት ለመፍጠር የሚያደርገውን ሴራ ለመቋቋም በአንድነት መቆም እንደሚገባ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ገለጹ፡፡